በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካውያን ህፃናት ጉዳይ አዲስ ዘገባ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አፍሪካውያን ልጆች በባሰ መልኩ ወደ ኋላ እየቀሩ በመሆናቸው እአአ እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ወይም በ 11 ዓመታት ውስጥ በዓለም በድኅነት ከሚኖሩት ሰዎች ከግማሽ በላይ ይሆናሉ ሲል አንድ አዲስ ዘገባ ጠቁሟል።

ይህ ማስጠንቀቅያ የወጣው የ 150 ሀገራት መሪዎች በዓለም ደረጃ ያለውን ድኅነት ለመቋቋም ስለሚችልበት መንገድ ለመነጋገር ኒውዮርክ በሚደረገው የተባበሩት መንግሥታስት ድርጅት የዘላቂ ልማት ጉባዔ ለመሳተፍ በሚዘጋጁባት ወቅት ነው። ጉባዔው በመጪው ረቡዕ ይጀመራል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ 17 የዘላቂ ልማት ግቦች ላይ ተስማምቷል። ቀዳሚ ቦታ የያዘው አስከፊ ድኅነትን እአአ እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ወይም በ 11 ዓመታት ውስጥ ማጥፋት የሚለው ነው።

ይሁንና ህፃናትን አድን የተባለው ድርጅትና የውጭ ልማት ተቋም ባወጡት ዘገባ መሰረት ዓለም ይህን ግብ አይመታም። የአፍሪካ ልጆችን ከድኅነት ለማውጣት በዓለም ቀፍ ደረጃ ሲደረግ የቆየው ጥረት ስኬት አላገኘም ማለት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG