በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት አረፉ


የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ቢዢ ካይድ ኢሴብሲ
የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ቢዢ ካይድ ኢሴብሲ

የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ቢዢ ካይድ ኢሴብሲ በዘጠና ሁለት ዓመታቸው አረፉ።

የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አንጋፋው ፖለቲከኛ ያረፉት ትናንት ምሽት ቱኒስ ወደሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ መሆኑን ገልጿል። ባለፈው ወርም በከባድ ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር መግለጫው አክሏል።

ኤሴብሲ በቱኒዚያ የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሪ ሲሆኑ ሥልጣን የያዙት እ ኤ አ በ2014 ማለትም ወደበርካታ የአረብ ሃገሮች በተዛመተው በቱኒዚያው ህዝባዊ ዓመፅ የረጅም ጊዜው አምባገነን ዚን ኤል አቢዲን ቤን አሊ ከሥልጣናቸው ከተወገዱ በኋላ ነው።

በሀገሪቱ ህግ መሰረት የፓርላማው አፈ ጉባዔ በጊዜያዊነት ይመራሉ። እ ኤ አ ጥቅምት ስድስት ምክር ቤታዊ ምርጫዎች ይካሄዳሉ። ከዚያም በኋላ ህዳር አስራ ሰባት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይከናወናል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG