በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ በድሮን ሽብር ስጋት ውስጥ እንደኾነች የቀጣናው የጸጥታ ተንታኞች ጠቆሙ


አፍሪካ በድሮን ሽብር ስጋት ውስጥ እንደኾነች የቀጣናው የጸጥታ ተንታኞች ጠቆሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

አፍሪካ በድሮን ሽብር ስጋት ውስጥ እንደኾነች የቀጣናው የጸጥታ ተንታኞች ጠቆሙ

በአፍሪካ፣ በአሸባሪ ቡድኖች ዘንድ፣ የሰው አልባ አሮፕላኖች(ድሮኖች) አጠቃቀም እየጨመረ እንደመጣ የጠቆሙ የጸጥታ ባለሞያዎች፣ የመንግሥት ኃይሎች በአንጻሩ፣ የአሸባሪዎቹን ውስብስብ ቴክኖሎጂ ልቀው ለመገኘት በሚያደርጉት ጥረት፣ አህጉሪቱን፥ የድሮን ሽብር እንደሚያሰጋት አስታውቀዋል።

ባለፈው ሳምንት ይፋ የተደረገው የባለሞያዎቹ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በአፍሪካ የሚገኙ አሸባሪ ቡድኖች፣ ድሮኖቹን አግኝተው እንደፍላጎታቸው ለማሻሻል፣ ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸውን እየተጠቀሙ ናቸው። ይኹንና፣ ድሮኖቹ እስከ አሁን፣ ጥቃት ለመሰንዘር አገልግሎት ላይ እንዳልዋሉ የጸጥታ ባለሞያዎቹ ገልጸው፣ ወደፊት ግን፣ የመንግሥታትን የኃይል ሚዛን ሊለውጡ እንደሚችሉ ያላቸውን ስጋት አመላክተዋል።

ቲሞቲ ኦቢየዙ ከአቡጃ ያደረሰንን ዘገባ፤ ስመኝሽ የቆየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG