በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ትራምፕ በአፍሪካ ላይ ያላቸው ፖሊሲ ግልፅ አይደለም


የአፍሪካ ካርታ
የአፍሪካ ካርታ

የዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጥ አፍሪካ ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

ከፍተኛው አሳሳቢ ጉዳይና ግልፅም ያልሆነው የሚስተር ትራምፕ ፖሊሲ የአፍሪካ ንግድና ግብይት ላይ ሊኖረው የሚቸለው ጫና ነው፡፡

አንዳንድ ገምጋሚዎች እንደሚሉትም ፕሬዚዳንታቸው የአፍሪካ መሪዎች በማህበራዊ ጉዳዮች ወደ ወግ አጥባቂነትን እንዲያቀኑ ያደርጋል፡፡

የቢሊዮነሩ ነጋዴ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት መመረጥ አንዳንዶችን ደስ አሰኝቷል፤ ሌሎች ደግሞ ተጨንቀዋል፡፡ በዚያም ሆነ በዚህ ዴንታ የሌላቸውም አሉ፡፡

የሆነው ሆኖ ሁሉም የአፍሪካ መሪዎች የዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚደንትነት በፖለቲካ በማህበራዊ ጉዳዮችና በኢኮኖሚ ምን አንድምታ እንደሚኖረው መጠየቃቸው አይቀሬ ነው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዘጋቢ ጂል ክሬክ ከናይሮቢ የላከችውን ትዝታ በላቸው ታቀርበዋለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በአፍሪካ ላይ ያላቸው ፖሊሲ ግልፅ አይደለም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:03 0:00

XS
SM
MD
LG