ከሠሀራ በመለስ ባሉት የአፍሪካ ሀገሮች ዙርያ 6 ጋዜጠኞች ተገድለዋል፤ 41 ደግሞ በእስር እየማቀቁ ነው።
ባለፈው ዓመት አፍሪካ ውስጥ 14 ጋዜጠኞች ተግድለው 34 ታስረዋል።
በዓለም ደረጃ ደግሞ በያዝነው ዓመት ቢያንስ 58 ጋዜጠኞች ተገድለዋል። ብዙዎቹ ግጭት በሚካሄድባቸው ሶርያ፣ ኢራቅ፣ የመን፤ ሊባያና አፍጋኒስታን የተገደሉ ናቸው።
90 ከመቶዎቹ የአካባቢዎቹ ተወላጆች ናቸው፤ በዓለም ዙርያ የታሰሩ ጋዜጠኞች ደግሞ 259 ይሆናሉ።
በ 16 ዓመታት ውስጥ ሲፒጄ ከመዘገበው አሀዝ የበዛ ነው።
ከአፍሪካ ለጋዜጠኞች አደገኛዋ ሃገር ሶማልያ ስትሆን ከታሰሩት 41 ጋዜጠኞች 33 ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚገኙ ናቸው።