በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

17 የአፍሪቃ ሃገሮች 50ኛ የነጻነት በአላቸውን እያከበሩ ነው


17 የአፍሪቃ ሀገሮች ካለፈው ሚያዝያ ወር እስከ ህዳር ባለው ጊዜ የነጻንት በአላቸውን እያከበሩ ነው ነው

17 የአፍሪቃ ሀገሮች ካለፍው ሚያዝያ እስከ መጪው ህዳር ወር ባለው ጊዜ 50ኛ የነጻነት በአላቸውን እያከበሩ መሆናቸው ይታወቃል። እነዚህ ሃገሮችም ሆኑ በአጠቃላይ በ1960 ዎቹና ከዚያ በፊት ነጻነታቸውን የተቀዳጁት የአፍሪቃ ሃገሮች ሁኔታ እንዴት እንደነበር ኋላስ ምን መልክ እንደያዘ እንዲያብራሩልን፣ በ City University of New York የአፍሪቃ ጥናትና ምርምር አስተማሪ የሆኑትን ዶክተር ገላውዲዮስ አርአያን ጋብዘናል።

የአፍሪቃ ሀገሮች በ1960 ዎቹና ከዚያም ቀድም ሲል ነጻነታቸውን ለማግኘት የበቁት "የአለም ጠቅላላ ሁኔታ በመቀየሩ ነው። ማለትም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ባኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መፈጠር እንዲሁም ጸረ ባርነት የነብሩት አሚርካና ሶቭየት ህብረት ተጽዕኖ ለአፍሪቃውያን ለነጻነት መነሳሳት ሁኔታ መንገድ ስለ ከፈተ ነው" ይላሉ ዶክተር ገላውዲዮስ።

XS
SM
MD
LG