በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ሲያሩ ቀበሌ በድሮን አድርሶታል በተባለው ጥቃት መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ሲያሩ ቀበሌ በድሮን አድርሶታል በተባለው ጥቃት መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ


የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ሲያሩ ቀበሌ በድሮን አድርሶታል በተባለው ጥቃት መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:23 0:00

የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ሲያሩ ቀበሌ በድሮን አድርሶታል በተባለው ጥቃት መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ሲያሩ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በድሮን አድርሶታል ያለውን ጥቃት በጥብቅ እንደሚያወግዙ በአፋር ክልል የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡ የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር እና የአፋር ለዴሞክራሲ እና ፍትሕ ፓርቲ በአወጡት መግለጫ፣ "ድርጊቱ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረገ እንዲሁም የሀገር ሉአላዊነትን የተዳፈረ ነው" ሲሉ ወንጅለውታል፡፡
በጥቃቱ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ዘጠኝ የሚኾኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው መግለጫውን
ካወጡት ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንደኛው ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል።

በሆስፒታሉ ውስጥ በድሮን ጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና በማግኘት ላይ መሆናቸውን የነገሩን የሲያሩ ቀበሌ
ነዋሪዋ ወ/ሮ መሬም መሐመድ ጥቃቱ በድንገት መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
በጥቃቱ የወ/ሮ መሬም እህትን ጨምሮ ሌሎችም መገደላቸውን የተጎጅዋ ቤተሰብ እንደሆኑ የገለጹልን አብደላ መሐመድ ጠቁመዋል፡፡

በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱት የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር እና የአፋር ለዴሞክራሲ እና ፍትሕ ፓርቲ ትናንት ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአወጡት የጋራ መግለጫ የጅቡቲ መንግሥት በአፋር ክልል ኤሊ ደአር ወረዳ ሲያሩ በተባለው ቀበሌ ላይ ፈጽሞታል ያሉትን የድሮን ጥቃት አውግዘዋል፡፡
በአፋር ክልል የሚገኘው የዱብቲ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሁሴን አደን በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ
ሆስፒታል የመጡና ህክምና በማግኘት ላይ የሚገኙ መኖራቸውን አረጋግጠዋል፡፡ የጅቡቲ የጸጥታ ኃይሎች በበኩላቸው “አሸባሪዎች” ብለው በገለጹት አማጺ ቡድን ላይ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ባደረጉት የድሮን ድብደባ ስምንት የቡድኑ አባላትን እና ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪሎችን መግደላቸውን ባለሥልጣናቱ እሑድ ዕለት አስታውቀዋል።
አዶራታ በተባለና ከኢትዮጵያ ድንበር ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የድሮን ጥቃቱ እንደተፈጸመ
የጅቡቲ የመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ አመልክቷል። “ስምንት አሸባሪዎች ተገድለዋል” ያለው መግለጫ፣ “ነገር ግን የሃገሪቱ ሲቪል ዜጎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል” ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG