በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ፣ ቻይናና ሩሲያ የባህር ኃይሎች ልምምድ

የሩሲያ የጦር መርከብ በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ በኬፕ ታውን መልህቁን ሲጥል፣ መርከቡ ወደ ደርባን ጉዞውን ለመቀጠል ነዳጅ ሊሞላ እንደቆመ አንድ የሩሲያ ዲፕሎማት መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
የሩሲያ የጦር መርከብ በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ በኬፕ ታውን መልህቁን ሲጥል፣ መርከቡ ወደ ደርባን ጉዞውን ለመቀጠል ነዳጅ ሊሞላ እንደቆመ አንድ የሩሲያ ዲፕሎማት መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የደቡብ አፍሪካ ባህር ኃይል ከቻይናና ከሩሲያ ባህር ኃይል ጋር የ10 ቀናት ልምምድ ዛሬ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

የባህር ኃይሎቹ ልምምድ የሚደረገው ሩሲያ ዩክሬንን የወረረችበት አንደኛ ዓመት በተቃረበበትና፣ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ከፍተኛ ትችት እያስተናገደች ባለበት ወቅት ነው።

ልምምዱን በማድረጓ “ደቡብ አፍሪካ በዩክሬን ላይ የተፈጸመውን ወረራና ጦርነት እንደምትደግፍ የቆጠራል” የሚል ነቀፌታ ከየአቅጣጫው በመሰማት ላይ ነው።

የሩሲያ የጦር መርከብ በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ በኬፕ ታውን መልህቁን ሲጥል፣ መርከቡ ወደ ደርባን ጉዞውን ለመቀጠል ነዳጅ ሊሞላ እንደቆመ አንድ የሩሲያ ዲፕሎማት መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በኬፕታውን ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዩክሬናውያን መልህቁን ወደጣለው የሩሲያ የጦር መርከብ ጀልባቸውን በማስጠጋት ከትናንት በስቲያ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

“ሞሲ” ብለው የሰየሙት የባህር ላይ ልምምድ (“ትስዋና” በተሰኘው የአካባቢው ቋንቋ “ጭስ” ማለት ነው) ደርባንና ሪቻርድስ ቤይ በተሰኙ የወደብ ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

የአሁኑ ልምምድ ከታቀዱት ተከታታይ የባህር ላይ ልምምዶች ሁለተኛው መሆኑ ታውቋል።

ከ350 በላይ የሚሆኑ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች በልምምዱ ላይ በመሳተፍ ከሩሲያና ቻይና ጋር ክህሎትና እውቀትን እንደሚለዋወጡ የአገሪቱ ሠራዊት ባለፈው ወር አስታውቋል።

ደቡብ አፍሪካ ገለልተኛ መሆንን በመምረጥ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ ከማውገዝ ተቆጥባለች፤ ጦርነቱ በንግግር እንዲፈታም ጠይቃለች።

XS
SM
MD
LG