በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ሰብአዊ እርዳታና የታሊባን መንግሥትነት


የአፍጋኒስታን ሴቶች በካቡል መብታቸው እንዲከበር ያደረጉት ሰልፍ እኤአ መስከረም 3 2021
የአፍጋኒስታን ሴቶች በካቡል መብታቸው እንዲከበር ያደረጉት ሰልፍ እኤአ መስከረም 3 2021

ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን የምታደርገው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አብቅቷል፡፡ ይሁን እንጂ “በታላቢን ቁጥጥር ሥር ያለውን የአፍጋኒስታንን ህዝብ መብት ለማስከበር የሚያስችሉ፣ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ አማራጮች አሉ” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩልም፣ የዩናይትድ ስቴትስ ከካቢኔ አባላት በአፍጋኒስታን ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገሩት የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን ፣ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ዛሬ ታሊባን ሙሉውን የካቡል አውሮፕላን ማረፊያና መላውን በሚባል መልኩ አፍጋኒስታንን ተቆጣጥሮታል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ የአፍጋኒስታን ሴቶች በሚጠይቁት የሰአብዊ መብት ጥያቄዎች ታሊባን ከወዲሁ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡

አገሪቱን እያጠቃ ያለው ከፍተኛ ድርቅም አፍጋኒስታን ያለ ዓለም አቀፉ እርዳታ እንደምን አድርጋ እንድምትችለው ጥያቄ እያስነሳ ነው፡፡

ምክንያቱም ዩናትይትድ ስቴት ታሊባንን እንደ አፍጋኒስታን መንግሥት አድርጋ በይፋ ገና አልተቀበለችውም፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ እንዲህ ይላሉ

"ከፌደራል መንግሥቱም አንድም ሰው አልተናገረም፣ ፕሬዚዳንቱም ሆኑ የመከላከያ ሚኒስትሩ ወይም ከደህንነትና የመረጃ ተቋማት ማህረሰብ ታሊባኖች ጥሩ ናቸው ብሎ የተናገረ አንድም ሰው የለም፡፡ አይደል? ያንን እያልን አይደለም፡፡ ለዚያ ነው እውቅና ለመስጠት አንጣደፍም ያልነው፡፡ የሚሆነውን በግልጽ እየተከታተልን ነው፡፡ ዓለም አቀፉን የግብይት ማዕከል ጨምሮ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ብዙ ነገሮች በእጃችን አሉ፡፡"

ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታን አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲከፈቱና የአፍጋንስታን ህዝብ በቀጥታ እርዳታ የሚያገኝበትን መንገድ እንዲመቻች እየሠራች መሆኑን ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ሰብአዊ እርዳታና የታሊባን መንግሥትነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:07 0:00


ለአፍጋኒስታን የሚሰጠው እርዳታ እየተጠና መሆኑንም፣ መግለጫውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይ ተናግረዋል፡፡

“ያ የሚወሰነው አዲስ በሚመሰረተው የአፍጋኒስታን መንግሥት ሁኔታ ይሆናል” ሲሉም አስረድተዋል፡፡
በተለይ በሴቶች በልጃገረዶች አነስተኛ ቁጥር ባላቸው የማህበረሰብ አባላት የሰአብአዊ መብት አያይዝ፣ እንዲሁም በጸረ ሽብርተኝነት አቋምና፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰ ጋር ባለው ግንኙነት " ይወሰናልም ብለዋል፡፡

በአፍጋኒስታን ከታሊባን ቁጥጥር ውጭ በሆነው፣ የፓንጅሺር ክፍለ ግዛት፣ በአህመድ ማሱድ የሚመሩት ጸረ ታሊባን ተዋጊዎች ሰሞኑን ከታሊባን ጋር ከፍተኛ ውጊያ እያካሄዱ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ተቃዋሚዎችን የመርዳት ፍላጎት እንደሌላት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) አስታውቋል፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ እንዲህ ብለዋል

“የአፍጋኒስታን ወታደራዊ ተልእኮ አብቅቷል፡፡”

በአፍጋኒስታ የቀሩ የመጨረሻ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ከወጡ ሁለት ቀናት በኋላ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ካቢኔ አባላት በአፍጋኒስታን ጉዳይ ለመጀመሪያ የተናገሩት የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን ፣ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል፡፡

በአሜሪካ ታሪክ ትልቁ የሆነውን ዜጎችንን በአየር ትራንስፖርት የማጓጓዝ ሥራ አሁን አገባደናል፡፡ በጀግንነት ነበር የተከናወነው፡፡ በጀግንነት ነበር፡፡

100 የሚደርሱ የአሜሪካ ዜጎች፣ በአፍጋኒስታን ወደ ኋላ መቅረታቸው ተነግሯል፡፡ አሜሪካውያንን ሲረዱ የነበሩ የተለይ ቪዛ አመልካቾችም እንዲሁ ከአገር አለመወጥታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ባለፈው ረቡዕ መግለጫቸው አምነዋል፡፡

አፍጋኒስታንን አሁንም የሚቆጣጠረው ታሊባን በመሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ጉዳይ ከታሊባን ጋር ተቀናጅታ መስራት የሚያስፈልጋት መሆኑን የዩናትድ ስቴትስ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ማርክ ሚሌ ተናግረዋል፡፡

ጀኔራሉ “ይህ ከድሮውም ጀምሮ ምህረት የሌለው ቡድን ነው መለወጥ አለመለወጡ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ አሁን ግን ዜጎችን ለማዳንና የሚደርስባቸውን አደጋ ለመቀነስ ማድረግ ያለብንን ነገር ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡”

ጦርነት ከባድ ነው፡፡ አረመኔና ጨካኝ ነው፡፡ ይቅር አያሰኝም፡፡ አዎ ሁላችንም ህመምና ቁጣ አለብን፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥም ሆነ ባለፉት 20 ቀናት ውስጥ የሆነውን ነገር ስናይ ህ መምና ቁጣን ይፈጥርብናል፡፡

በሌላም በኩል ከአፍጋኒስታን እንዲወጡ ተደርገው በአውሮፓ የሚገኙ የአፍጋኒስታን ዜጎችን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የማጓጓዙ ሥራ ግን ተጠናክሮ መቀጠሉን ፔንታገን አስታውቋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስትን ስለዚሁ ሲናገሩ

“አሁን በየቀኑ አምስት ወይም ስድስት መቶ ሰዎችን ማጓጓዝ የምንችልበት ሁኔታ ላይ እየደረስን ነው፡፡ ካሁን በኋላ በየቀኑ 2ሺ500 እስከ 3ሺ ሰዎች ማጓጓዝ የምንችልበት ደረጃ መድረስም እንችል ይሆናል፡፡” ብለዋል፡፡

መካለከያ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በቦምብ ፍንዳታ 13 አሜሪካውያንና 170 የአፍጋኒስታን ዜጎችን የገደሉትን በአፍጋኒስታን የሚገኙትን የአይሲስ አሸባሪ ቡድኖች ተገቢ ነው ብለው በሚያስቡበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትበቀል አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG