በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓኪስታን በአፍጋኒስታን ላይ ባደረሰችው ጥቃት አንድ ሲቪል ህይወቱ አለፈ

ፓኪስታን፣ ከአፍጋኒስታን ጋር በሚያዋስናት ምሥራቅዊ ኩናረ ክፍለ ሃገር ውስጥ ባደረሰችው ጥቃት አንድ ሲቪል መሞቱን የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ፓኪስታን፣ ከአፍጋኒስታን ጋር በሚያዋስናት ምሥራቅዊ ኩናረ ክፍለ ሃገር ውስጥ ባደረሰችው ጥቃት አንድ ሲቪል መሞቱን የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

አንድ የክፍለ ሀገሩ መንግሥታዊ ቃልአቀባይ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ የፓኪስታን ወታደሮች ባለፉት ሃያ አራት አራት ሰዓታት ሳረካኖ እና ዳንገነ በተባሉ የአፍጋኒስታን የድንበር ከተማዎች ላይ፣ ከመቶ በላይ የአዳፍኔ ተኩስ ማካሄዳቸውን አመልክተዋል።

ቃልአቀባዩ ጋኒ ሞሰሚ አክለው እንደተናገሩት፤ ተኩሱ በርካታ የሲቪሎችን መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።

በጉዳዩ ላይ እስካሁን ከፓኪስታን ጦር ኃይልም ሆነ ከመንግሥት በኩል የተሰጠ መልስ አልተሰማም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG