በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን አፍጋኒስታንን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት አባልነት አስወጣ 


የታሊባኑን መንፈሳዊ መሪ ሂባቱላህ አክሁንዳዛዳ ፖስተር፤ በካቡል እአአ ነሃሴ 14/2023
የታሊባኑን መንፈሳዊ መሪ ሂባቱላህ አክሁንዳዛዳ ፖስተር፤ በካቡል እአአ ነሃሴ 14/2023

የአፍጋኒስታኑ ኃይማኖታዊ አክራሪ ቡድን ታሊባን መሪዎች በዛሬው ዕለት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2003 ሀገሪቱን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት የተቀበለውን የሄጉን ችሎት የምሥረታ ስምምነት ተፈጻሚ ያደረገ ውሳኔ "ሕጋዊነት የለውም" ሲሉ ውድቅ አደረጉ። ታሊባን የወሰደው ይህ ርምጃ ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት (አይሲሲ) በአባል አገራት ላይ ያለውን የዳኝነት ሥልጣን ተቀባይነት የሚነፍግ ነው።
ውሳኔው ባለፈው ወር የአይሲሲ ዋና አቃቤ ሕግ የታሊባኑን መንፈሳዊ መሪ ሂባቱላህ አክሁንዳዛዳ እና የቅርብ ረዳታቸውን “የአፍጋኒስታንን አዳጊ ሴቶች እና አዋቂ ሴቶች በማዋከብ ተጠያቂ ናቸው” ሲል ያወጣውን የእስር ማዘዣ ካወጣ በኋላ ነው።
ዓለም አቀፍ እውቅና የነበረውን የአፍጋኒስታን መንግሥት መንኮታኮት ተከትሎ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ነሐሴ 2021 ታሊባን ወደ ሥልጣን በመጣበት ወቅት ሁለት ዐስርት ዓመታት የዘለቀውና በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው የኔቶ ጦር የአፍጋንስታን ቆይታም ተቋጭቷል።

በአሁኑ ወቅት እስላማዊውን መንግሥት እየመራ ያለው ታሊባን፣ ጥብቅ እስላማዊ የሸሪዓ ሕግ ተፈጻሚ በማድረግ በንግግር ነፃነት፣ በሴቶች የትምህርት ተደራሽነት እና በማህበረሰቦች ሕዝባዊ ሚናዎች ላይ ሰፊ ገደቦችን መጣሉ ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG