በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን አፍጋኒስታንና ኢንዶኔዢያ ጎርፍ ከ300 በላይ ሰዎች ገደለ


በባግላን፣ ሰሜን አፍጋኒስታን በምትገኘው አውራጃ በተፈጠረው ድንገተኛ ጎርፍ ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ
በባግላን፣ ሰሜን አፍጋኒስታን በምትገኘው አውራጃ በተፈጠረው ድንገተኛ ጎርፍ ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ

ባግላን በተባለችውና በሰሜን አፍጋኒስታን በምትገኘው አውራጃ በተፈጠረው ድንገተኛ ጎርፍ ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ከ1ሺሕ በላይ ቤቶችም መውደማቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

ያለተለመደውን ከባድ ዝናብና ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የተፈጠሩት በርካታ ጎርፎች ጉዳት ማድረሳችውን ትከትሎ፣ ድርጅቱ ከአደጋው ለተረፉት ምግብ በማከፋፈል ላይ መሆኑንም አስታውቋል።

የታሊባን መንግስት ቃል አቀባይ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባወጡት መልዕክት፣ በመቶዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል በኢንዶኔዢያ፣ ሱማትራ በተባለችው ደሴት ከባድ ዝናብ፣ ቀልጦ የቀዘቀዘ የእሳተ ገሞራ ፍሳሽ እና የጭቃ ናዳ ባስከተለው አደጋ 37 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችም የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።

ጎርፉ ሰዎችን ሲወስድ፣ ከመቶ በላይ ቤቶችንም አስምጧል።

የቀዘቀዘው የእሳተ ገሞራ ፍሳሽ በዝናብ ወቅት ጠጠርና ሌላም ቀላቅሎ ቁልቁል ሲወርድ አደጋ ሊያስከትል ችሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG