በምዕራብ አፍጋኒስታን፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች እንደሞቱ፣ የታሊባን ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።
መንቀጥቀጡ፣ በሬክተር መለኪያ 6ነጥብ3 መጠን እንዳለው ተገልጿል። ዋናውን መንቀጥቀጥ ተከትሎ በድኅረ ርዕደቱ በርካታ ሰዎች እንደሞቱ ታውቋል።
የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀሰውም ሊበልጥ እንደሚችል፣ የታሊባን ባለሥልጣናት እየተናገሩ ናቸው።
የተመድ የሰብአዊ መብቶች ማስተባበሪያ ቢሮ እንዳስታወቀው፣ መንቀጥቀጡ ስምንት መንደሮችን ሲያዳርስ፣ 1ሺሕ300 ቤቶችን አውድሟል።
ሰዎች፣ ከሕንጻዎች ርቀው መንገድ ላይ መተኛት እንደጀመሩና በቂ ርዳታም እያገኙ እንዳልኾነ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም