በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን ወታደራዊ ሰፈር በደረሰው ጥቃት ቢያንስ 40 የፀጥታ ኃይል አባላት ተገድለዋል


ታሊባን ዛሬ ሊነጋጋ ሲል በሰሜን አፍጋኒስታን በሚገኝ ወታደራዊ ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 40 የፀጥታ ኃይል አባላት ተገድለዋል።

ታሊባን ዛሬ ሊነጋጋ ሲል በሰሜን አፍጋኒስታን በሚገኝ ወታደራዊ ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 40 የፀጥታ ኃይል አባላት ተገድለዋል። በሀገሪቱ ዙርያ የሚካሄዱት የአማጽያን ጥቃቶች በመንግሥት ኃይሎች ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሱ ናቸው።

ከሞቱት መካከል 31 የሀገሪቱ ብሄራዊ ሰራዊት ወታደሮችና ዘጠኝ ፖሊሶች እንደሚገኙባቸው አንድ ስማቸውን መገለጽ ያልፈለጉ ጥቃቱ በተፈጸመበት አከባቢ ያሉ የፀጥታ ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የታሊባን ቃል አቀባይ በጥቃቱ ሁለት ወታደራዊ ሰፈሮችን ማርከናል። እስከ 70 የሚደርሱ ወታደሮችን ገድለናል ይላል። ብዙውን ጊዜ አማፅያን ያገኙትን ስኬት የማጋነን ልምድ እንዳልቸው ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG