ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን በሚገኘው ትልቁ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሰፈር ላይ ዛሬ በፈነዳው ከባድ ቦምብና በተከፈተው የተኩስ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አብዛኞቹ ሲቪሎች መሆናቸው ታውቋል።
የሀገሪቱ ወታደራዊ ባለሥልጣኖች በገልጹት መሰረት፣ አንድ አጥፍቶ ጠፊ፣ ፓርዋን በተባለው ክፍለ-ሀገር በሚገኘው፣ ባግራም የአውሮፕላን ማረፍያ አጠገብ ባለ፣ የማይሰራ ሆስፒታል በር ላይ፣ በፈንጂ የተሞላ መኪናን አፈነዳ። ታሊባን ለጥቃቱ ሃላፊነት ወስዷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ