በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ልዩ መርማሪው አፍጋኒስታን እንዳይገቡ ታገዱ


በአፍጋኒስታን የታሊባን መሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ልዩ መርማሪ ሪቻርድ ቤኔት
በአፍጋኒስታን የታሊባን መሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ልዩ መርማሪ ሪቻርድ ቤኔት

በአፍጋኒስታን የታሊባን መሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ልዩ መርማሪ የሆኑትን ሪቻርድ ቤኔት “ፕሮፖጋንዳ አሰራጭተዋል” በሚል ወደ ሃገሪቱ እንዳይገቡ አግደዋል።

የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላ ሙጃሂድ እንዳሉት ተመድን የሚወክሉት መርማሪ “በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ” ያዛባሉ፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረስብም “አሳሳች መልዕክት ያቀርባሉ ሲሉ ከሰዋል።

ከሁለት ዓመታት በፊት ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ ሪቻርድ ቤኔት በተደጋጋሚ ወደ ካቡል በመጓዝ የሃገሪቱን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በተመለከተ ጀኒቫ ለሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብት ም/ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብት ም/ቤትም ሆነ ሪቻርድ ቤኔት ወደ አፍጋኒስታን እንዳይገቡ መከለከላቸውን በተመለከተ ወዲያውኑ አስተያየት አልሰጡም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG