በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን የታሊባን ግስጋሴና የስደተኞች እጣ


አፍጋኒስታን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ መዲናዪቱ ካቡል ከመጡ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከል
አፍጋኒስታን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ መዲናዪቱ ካቡል ከመጡ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከል

የአፍጋኒስታን ነዋሪዎችና ቤተሰቦች መላውን አፍጋኒስታንን ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ ያሉትን የታሊባንን ኃይሎች እየሸሹ ነው፡፡ አንዳንድ ስደተኞችም ከተወሰነው የሞት አደጋ ቢያመልጡም የወደፊት ህይወት እጣ ፈንታቸው እርግጠኞች መሆን እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ታሊባኖች ዛሬ ባወጡት መግለጫ ምሽቱን ባካሄዱት ጥቃት በአፍጋኒስታን ሁለተኛዪቱን ትልቅ ከተማ ደቡባዊ ካንደሃርን ና ጨምሮ በሰሜን ምስራቅና ደቡብ ያሉትን አምስት ዋና ዋና ከተሞችን ሙሉ ለሙሉ መቆጣራቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአፍጋኒስታን መንግሥት የታሊባንን መግለጫ ባያስተባብልም፣ ታሊባኖች በሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሳዩትን ግስጋሴ የመንግሥቱ ጸጥታ ኃይልሎች ለመቆጣጠር የተቸገሩ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስትር ቤን ዋላስ ደግሞ ዛሬ ከስካይ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ አፍጋኒስት የፈረሰች አገር የመሆን አደጋ እንደተደቀነባት ገልጸው “አልቃይዳ እንደገና ተመልሶ በአገሪቱ ሊንሰራፋ ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

በአፍጋኒስታን የታሊባን ግስጋሴና የስደተኞች እጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:10 0:00


የታሊባን ኃይሎች፣ የአፍጋኒስታንን መንደሮች፣ ትናንሽ እና ትላልቅ ከተሞች እየተቆጣጠሩ ነው፡፡ አብዛኞቹ የአፍጋኒስታን ነዋሪዎችና ቤተሰቦችም፣ ጦርነቱን እና እየከፋ የመጣውን ድህነት በመሸሽ፣ የኢራን እና የቱርክ ድንበርን እያሳበሩ በመሸሽ ላይ ናቸው፡፡

ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በቱክር ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የቫን ሐይቅ ውስጥም፣ ስደተኞችን ደብቀው በሚያጓጉዙ ፍርስራሽ ጀርልባዎችም ውስጥ፣ ሞተው የተገኙ ስደተኞች መኖራቸውም ተዘግቧል፡

፡ ታሊባኖች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች፣ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው፣ ወይም ከውጭ ድርጅቶች ጋር የሚሰራ፣ ወይም የኻዛራ ብሄረሰብ አባል የሆነ ሰው ሊገደል ስለሚችል ህይወቱ አደጋ ላይ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የቀድሞ የአፍጋኒስታን ወታደራዊ አዛዥ የነበሩት ፋሪድ ባረካዚ ፣በታሊባኖች ከነሱ ጋር እንዲቀላቀሉ ተጠይቀው እምቢ በማለታቸው፣ ወይ አገር ለቀው መውጣት ወይም ሊገደሉ እንደሚችሉ የተነገራቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡

“አፍጋኒስታን ትልቅ ጥፋት አለ፡፡ አሁንማ እየባሰበት ነው፡፡ ብዙ ክፍለግዛቶች በታሊባን ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡”

እየተካሄደ ያለው ጦርነት፣ ብዙ የንግድ ድርጅቶችና ትምህር ቤቶችን እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ የታሊባን ኃይሎችም፣ እስላማዊ ህግን ማስተዋወቅ ጀምረዋል፡፡ የቀድሞ የዩኒቭርስቲ ተማሪ የሆነው ቃሲም ዩሴፊ እንዲህ ይላል

በታሊባን ብዙ ማስፋራሪያዎች ጥቃቶች ደርሰውብናል፡፡ ከዩኒቨርስቲያችን ብዙዎቹ መምህራንና ጓደኞቻችን ተገድለዋል፡፡

ታሊባኖች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች የሚኖሩ፣ በርካታ ልጃገረዶችና ሴቶች፣ ገና ካሁኑ፣ እኤአ በ1990ዎቹ ውስጥ እንደነበሩት ሆነው እንዲኖሩ መገደዳቸውን እየተናገሩ ነው፡፡

የቀድሞ የቋንቋ መምህር የሆኑት፣ ሊያን ሳዴት እንዲህ ይላሉ

በዚህ ጊዜ እንኳ ሴቶች ወደ ህዝባዊ ዝግጅቶችም ሆነ ለትምህርት መውጣት አይችሉም፡፡ ምክንያቱን ደህንነታቸው የተጠበቀ አይደለም፡፡

ወደ ቱርክ የተሰድዱትም በመንገድ ብዙ ችግር እንዳገኛቸውና የሰአብዊ እርዳታ ለማግኘት ብዙ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ያናገራሉ፡፡

ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው በመሆኑ በመንገድ የተያዙ የተደበደቡ ከዚያም የከፋ ችግር የደረሰባቸውና ወደ መጡበት ተመልሰው የተባረሩም በርካቶች መሆኑን ተገልጿል፡፡

ከጓደኖቻቸው ጋር 1ሺ500 ኪሎሜትር ተጉዘው ስታንቡል የገቡት ባረከዜ የተባሉ ስደተኛ፣ “ይህን ባውቅ ኖሮ ከአፍጋኒስታን አልወጣም ነበር” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አፍጋኒስታንን ለቆ መውጣቷን ካሳወቀች በኋላ የታሊባን ኃይሎች ይዞታቸውን እያጠናከሩ ነው፡፡ ከ34 የአፍጋኒስታን ክፍለ ግዛቶች 16 ያህሉን መቆጣጠራቸው ተመልክቷል፡፡

በተለይ በዚህ ሳምንት ውስጥ ብቻ በአፍጋኒስታን ሁለተኛዪቱን ትልቅ ከተማ ደቡባዊ ካንደሃርን እና እንዲሁም ከዋና ከተማው ካቡል 150 ኪ.ሜ ላይ የምትገኘው ጋዛኒ ከተማ ጋር ወደ አምስት ትላላቅ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአፍጋኒስታን መንግሥት ስለ ሁኔታው ማረጋጋጫ ባይሰጥም መላውን አፍጋኒስታን ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ ያሉትን ታሊባኖችን ለማስቆም መቸገሩ እየተነገረ ነው፡፡

በካቡል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፣ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የታሊባን ኃይሎች፣ በርካታ የአፍጋኒስታን መንግሥት የሲቪል ሠራተኞችና የጸጥታ ባለሥልጣናትን፣ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ፣ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አውግዟል፡፡

ኤምባሲው በመግለጫው “ እነዚህ ድርጊቶች ተቀባይነት የሌላቸው ከመሆኑንም ሌላ፣ ታሊባን በዶሃው እየተካሄደ ያለውን የሰላም ስምምነት፣ ለመደገፍ ከገባው ቃል ጋር የሚቃረኑ ናቸው” ብሏል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ፣ባላፈው ረቡዕ በዋሽንግተን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “ዩናይትድ ስቴትስ እየተባባሰ የመጣውን የአፍጋኒስታንን ሁኔታ ትገነዘባለች” ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አያይዘውም “የአሁኑ ትኩረታችን፣ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ አፍጋኒስታንን በሰላም፣ ሙሉ ለሙሉ ለቀን የምንወጣበትና፣ የአፍጋኒስታን ኃይሎችን የአየር ላይ ድጋፍ መስጠት የምችልባቸውን መንገዶች፣ የትና በምና ሁኔታ እንደሆኑ ማየት ነው” ብለዋል፡፡ አሁን እያደረግን ያለነውም እሱን በማለትም አክለዋል፡፡

የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስትር ቤን ዋላስ ዛሬ ከስካይ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ አፍጋኒስት የፈረሰች አገር የመሆን አደጋ እንደተደቀነባት ገልጸው “አልቃይዳ እንደገና ተመልሶ በአገሪቱ ሊንሰራፋ ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ዋላስ ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫም በአፍጋኒስታን የሚገኙ 4ሺ የእንግሊዝ ወታደሮችንና እንግሊዞችን ሲረዱ የቆዩ ወደ 2ሺ የሚደርሱ የአፍጋኒስታን ዜጎችን፣ ከታሊባን ጥቃት ለመታደግ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፓራትሩፐሮችን ወደ ካቡል ለመላክ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል፡፡

(የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዎች ካጠናቀሯቸው ዘገባዎች የተወሰደ

XS
SM
MD
LG