በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኢራን ይሰልል ነበር የተባለ ጥምር ዜግነት ያለው ግለሰብ ታሰረ

የጀርመንና የአፍጋኒስታን ጥምር ዜግነት ያለው ግለሰብ ጀርመን ውስጥ ለኢራን ይሰልል ነበር ተብሎ መታሰሩ ተገለፀ። ግለሰቡ በጀርመን ጦር ኃይል ውስጥ ይሰራ እንደነበርም የጀርመን ፌዴራል ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።

የጀርመንና የአፍጋኒስታን ጥምር ዜግነት ያለው ግለሰብ ጀርመን ውስጥ ለኢራን ይሰልል ነበር ተብሎ መታሰሩ ተገለፀ። ግለሰቡ በጀርመን ጦር ኃይል ውስጥ ይሰራ እንደነበርም የጀርመን ፌዴራል ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።

የ50 ዓመቱ ተጠርጣሪ አብዱል ሀሚድ ዛሬ ማክሰኞ ፍ/ቤት እንደሚቀርብም ታውቋል።

ዐቃቤ ህግ በሰጡት ቃል፣ ተጠርጣሪው በጀርመኑ ጦር ኃይል ውስጥ በቋንቋ ገምጋሚነትና በባህል ጥናት ውስጥ ሲሰራ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን እያሾለከ ለኢራን ያቀብል እንደነበር ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG