ዋሺንግተን ዲሲ —
ማዕከላዊ ምሥራቅ አፍጋኒስታን ውስጥ በደረሰ የሮኬት ፍንዳታ፣ ብዙዎቹ ሕፃናት ያሉባቸው ሰባት ሲቪሎችን ገደለ፣ ሌሎች ሦስት አቆሰለ።
ጋሃዘኒ ክፍለ ሀገር ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ማን ኃላፊ እንደሆነ፣ አወዛጋቢ የሆኑ ዘገባዎች እየተሰሙ ናቸው።
አንድ የክፍለ ሀገሩ መንግሥታዊ አስተዳደር ቃልአቀባይ ለቪኦኤ እንደተናገረው፣ ለበርካታ ሲቪሎች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት ቃራ ባጊ መንደር ላይ ያደረሰው ታሊባን ነው።
የጋሃዘኒ ክፍለሀገር ምክር ቤት አባል ሃሰን ረዛ ዩሱፍ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ ፀረ አማጽያን ጥቃት እየተካሄደ ባለበት ወቅት፣ የአፍጋኒስታን ኃይሎች የአየር ጥቃት በሲቪሎች መድረሱን አመልክተዋል።
ይኸኛው ጥቃት ደግሞ፣ ሰባት ህፃናትና አንዲት ሴት መግደሉ ታውቋል።
ለጥቃቱ ተጠያቂ ታሊባን ነው የተባለውን የባለሥልጣናቱን አባባል ቡድኑ ውቅድ ማድረጉም ተሰምቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ