በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ


አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ዛሬ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ በርካታ ዕጩዎች የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሃሚድ ካርዛይና የሃገሪቱ መሪ አብዱላ አብዱላ በተገኙበት ስብሰባ ላይ የከባድ መሣሪያ ጥይቶች ተኩሰዋል።

ታጣቂዎቹ ዛሬ ጥቃቱን ባደረሱበት ወቅት አብዱላ - ለተሰብሳቢው ሕዝብ ንግግር በማድረግ ላይ ነበሩ ተብሏል። ወንጀል ብለውታል ጥቃቱን።

ጥቃቱ የደረሰው በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ የሒዝቢ ኢ ዋህዳት ኢ ኢስላም ፓርቲ አባላት፣ መሪያቸው አብዱል አሊ ማዛሪ የተገደሉበትን 24ኛ ዓመት መታሰቢያ በማክበር ላይ ነበሩ።

በዛሬው ጥቃት ቢያንስ አንድ ሰው ተገድሎ ሌሎች 16 መቁሰላቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር አውሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG