ዋሺንግተን ዲሲ —
ዛሬ ሰሜን አፍጋኒስታን ውስጥ የታሊባን ታጣቂዎች እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሰዎች በአጀብ ይጓዙ የነበሩ አውቶቡሶች ላይ የነበሩ ብዛት ያላቸው ተሳፋሪዎችን አገቱ።
የኩንዱዝ ክፍለ ሃገር አስተዳደር ቃል አቀባይ እንዳሉት አውቶቡሶቹ ከአጎራባች ክፍለ ሀገር ወደዋና ከተማዋ ወደካቡል በመጓዝ ላይ ሳሉ ታጣቂዎቹ አስቁመው መንገደኞቹን አስወርደው የወሰዷቸው። ታሊባን ለዚህ ተግባር ሃኃላፊነት አልወሰደም።
ይህ ጥቃት የደረሰው የአፍጋኒስታን ፕሬዚደንት አሽራፍ ጋኒ በበኩላችን ከታሊባን ጋር ለሶስት ወራት ተኩስ አቁም እንደረጋለን ሲሉ ባወጁ በማግስቱ መሆኑ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ