በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍጋኒስታን ከቻይና ጋር የአየር በረራ ግንኙነት ጀመረች

የባሕር በር የሌላት አፍጋኒስታን፣ 200 ኩንታል የጫነ ካርጎ በመላክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ጋር የአየር በረራ ግንኙነት ማድረጓ ተገለጸ።

የባሕር በር የሌላት አፍጋኒስታን፣ 200 ኩንታል የጫነ ካርጎ በመላክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ጋር የአየር በረራ ግንኙነት ማድረጓ ተገለጸ።

የአፍጋኒስታኑ ፕሬዚደንት አሻራፍ ጋኒ እና የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ዛሬ ካቡል ውስጥ የተከናወነውን ሥነ ሥርዓት መከታተላቸው ታውቋል።

የአየር ግንኙነቱ መጀመር፣ ወደፊት የአፍጋኒስታንን ትኩስ የፍራፍሬ ምርቶችን ለቻይና ገበያ ለማቅረብ የሚረዱ ኮሪደሮችን እንደሚፈጥር ተስፋ ተደርጓል።

ከዚህ ቀደም አፍጋኒስታን የአየር ኮሪደሮቿን ክፍት ያደረገችው ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከካዛኪስታን፣ ከኢንዶኔዥያና ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር እንደነበረ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG