በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍጋኒስታን ሴቶች ወንዶች ብቻ በሚሳተፉበት ተቃውሞ ለመካፈል ወሰኑ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የአፍጋኒስታን ሴቶች ዛሬ ማክሰኞ በወግ አጥባቂዋ ሂለማንደ ክፍለ ሀገር ውስጥ በሚካሄደውና ወንዶች ብቻ በሚሳተፉበት የመቀመጥ ተቃውሞ አድማ ለመካፈል መወሰናቸው ተሰማ።

የአፍጋኒስታን ሴቶች ዛሬ ማክሰኞ በወግ አጥባቂዋ ሂለማንደ ክፍለ ሀገር ውስጥ በሚካሄደውና ወንዶች ብቻ በሚሳተፉበት የመቀመጥ ተቃውሞ አድማ ለመካፈል መወሰናቸው ተሰማ።

የተቃውሞው ዓላማ፣ ከታሊባን ጋር ያለው ጠላትነት እንዲቆም የሚጠይቅ ሲሆን ሰልፈኛው ወደ ታሊባን ምሽግ እያመራ እንደሆነም ታውቋል።

ተቃውሞውን ወንዶቹ የጀመሩት፣ ባለፈው ሐሙስ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በክፍለ ሀገሪቱ ከተማ ላሽካርጋን ያደረሰው ጥቃት ስላስቆጣቸው መሆኑም ታውቋል።

ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ፍንዳታው ቢያንስ 14 ሰዎችን ገድሎ ሌሎች ከአርባ በላይ አቁስሏል።

ብዙዎቹ ተቃዋሚ ሴቶች ባለቤቶቻቸውን በጦርነቱ ያጡ መሆናቸውም ተገልጧል።

ሰልፈኛው ከነገ ወዲያ ሐሙስ፣ የአማጺው ቡድን ምሽግ ወደሚገኝበት ወደ ሙሳ ቀለ እንደሚያመራ፣ ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ተቃውሞ ሰልፍ ያዘጋጁት ወገኖች ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG