በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታሊባን ሽምቅ ተዋጊዎች አሥራ አንድ የአፍጋኒስታን ወታደሮችን ገደሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የታሊባን ሽምቅ ተዋጊዎች ምዕራብ አፍጋኒስታን ውስጥ አንድ የመንግሥቱን የፀጥታ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አጥቅተው በትንሹ 11 ወታደሮችን ገድለዋል።

የታሊባን ሽምቅ ተዋጊዎች ምዕራብ አፍጋኒስታን ውስጥ አንድ የመንግሥቱን የፀጥታ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አጥቅተው በትንሹ 11 ወታደሮችን ገድለዋል።

ትላንት ማታ በሔራት ክፍለ ሃገር በሺንዳንድ አውርጃ ጥቃቱ የደረሰበት የፀጥታ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከኢራን ጋር ይዋሰናል።

የአውራጃው ዋና አስተዳዳሪ ሹክሩላህ ሻከር ለቪኦኤ ሲናገሩ በታሊባኑ ጥቃት ሌሎች አራት የመንግሥቱ ወታደሮችም ቆስለዋል።

የሕግና ሥርዓት አስከባሪ ፖሊስ በመባል የሚታወቀው ጣቢያ ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ጥበቃውን ያደርጉ የነበሩት የአፍጋኒስታን ወታደሮች ነበሩ ተብሏል።

ከሞቱት መካከልም የጣቢያው አዛዥ ሳዒድ ሻራፉዲን አላዊ ይገኙበታል ሲሉ የአውራጃው ዋና አስተዳዳሪ ሹክሩላህ ሻከር አክለው ተናግረዋል።

የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቡላህ ሙጃሂድ ለመገናኛ ብዙሃን ባሠራጩት መግለጫ በጥቃቱ የተገደሉት የመንግሥት ወታደሮች ከ20 እንደሚበልጡና 4 ሃምቪ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ይዘው መሄዳቸውን ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG