ዋሺንግተን ዲሲ —
ዛሬ በደረሰው ጥቃት 24 ሰዎች ተገድለው ከ30 በላይ ቆስለዋል። አንድ ሞተር ቢስክሌት የሚነዳ አጥፍቶ ጠፊ፣ ሰው በተሰበሰበበት ወታደራዊ ቦታ አጠገብ ፈንጂውን ሲያፈነዳ ፕሬዚዳንቱ ንግግር ለማደረግ ቀርበው እንደነበር ተዘግቧል። ህንፃው ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ጉዳት የደረሰበት የለም። የምርጫ ዘመቻውም ከጥቃቱ በኋላ ቀጥሏል ሲሉ የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስራት ራሂሚ በትዊተር ጠቁመዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ