ዋሺንግተን ዲሲ —
ፓኪስታን በዩናይትድ ስቴትስና በታሊባን መካከል ዛሬ በተባበረው የአረብ ኤሚሬቶች የሰላም ሥምምነት እንዲካሄድ አስተባባራለች። ዓላማው በአፍጋኒስታን የሚካሂደው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ለመጣር ነው።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋይሳል ኢስላማባድ ከሌሎች ማኅበረሰቦችና የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በጦርነት በደቀቀችው ጎረቤት ሀገር ሰላምና እርቅ እንዲወርድ ለመጣር ቁርጠኛ ናት ብለዋል።
ድርድሩ በተባበረው የአረብ ኤሚሬቶች መዲና አቡ ዳቢ ከመጀመሩ በፊት “ይህ ንግግር ደም መፋሰሱን አቁሞ በክልሉ ሰላም ያመጣል የሚል ተስፋ አለን” የሚል አጭር መግለጫ ሰጥተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ