በመንዝና ግሼ አውራጃ፣ ኤፍራታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሳስንቅ ገብርኤል በተባለው ቦታ ከአባታቸው ከቀኛዝማች ኃይለማርያም ወልደገብርኤል፣ ክእናታቸው ከወ/ማሚቴ ወይም ስፍራሽ ብዙ ገብረ ሥላሴ ታኅሣሥ 5 ቀን፣ 1919 ዓ.ም የተወለዱት አፈ ንጉሥ ተሾመ፣ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተሾሙ፣ የመጀመሪያው ባለ ዲግሪ የጠቅላይ ንጉሠ ነገሥቱ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ነበሩ።
ከኮከበ ጽባሕ 2ኛ ደረጃ በኋላ የቀኃሥ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የነበሩት አፈ ንጉሥ ተሾመ፣ በ1958 ዓ.ም ከሞንትሪያሉ የካናዳው /McGill Universitty/ የህግ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አፈ ንጉሥ ተሾመ ኃይለማራም፣ የሦስት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆኑ፣ የሴት ልጃቸውን ልጅ በማየት አያትም ለመሆን በቅተዋል።
ከቤተሰብና ከወዳጆቻቸው ባገኘንው መረጃ መሠረት፣ የአፈ ንጉሥ ተሾመ ኃ/ማርያም የቀብር ሥነ ሥርዓት፣ ከነገ ወዲያ አርብ እዚሁ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ይፈፀማል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ