ድሬዳዋ —
የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን አራት ነዋሪዎች መገደላቸውንና ሁለት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ገለፀ፡፡ የዞኑ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር መሐመድ አብዱላሂ ጣሊብ ለቪኦኤ እንደገለፁት የአፋር ልዩ ኃይሎች ከሁለቱ ክልሎች ድንበር ርቆ ወደሚገኘው ገብለሉ ወረዳ ገብተው ነው ይሄንን ጥቃት የፈፀሙት፡፡
በሦስት አወዛጋቢ ቀበሌዎች የተነሳ ግጭት ውስጥ የገቡት አፋር እና ኢሳ ሶማሌ ላለፉት ሳምንታት ሰላም ርቋቸው ነው ቆይቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ