በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነዋሪዎች ጥቃት እና መፈናቀል የአፋር እና የሶማሌ ክልሎችን እያወዛገበ ነው


የነዋሪዎች ጥቃት እና መፈናቀል የአፋር እና የሶማሌ ክልሎችን እያወዛገበ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:07 0:00

የነዋሪዎች ጥቃት እና መፈናቀል የአፋር እና የሶማሌ ክልሎችን እያወዛገበ ነው

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፣ በአፋር ክልል ውስጥ ጥቃት እየፈጸሙ ነው፤ ሲሉ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናገሩ፤ በጥቃቱም፣ አርብቶ አደሮች ከፍተኛ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ገልጸዋል።

ከሶማሌ ክልል ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የክልላቸውን ወሰን አልፎ እስከ አፋር ክልል የደረሰ የልዩ ኃይል ወታደራዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩን በመጥቀስ ያስተባብላሉ።

በአፋር ክልል ውስጥ በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ላይ በሚነሣ የይገባኛል ውዝግብ ምክንያት፣ ተደጋጋሚ ግጭቶች እየተከሠቱ ሲኾን፤ በሶማሌ ክልል በኩል አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪዎች፣ ከእነዚኽ ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ ሲሉ ወቀሳ ያሰማሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የሕግ ባለሞያ፤ ከግጭት ይልቅ ሕጋዊ አማራጮችን መከተል የተሻለ መፍትሔ እንደሚያስገኝ ይመክራሉ።

በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG