በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፋር ክልላዊ መንግሥት ለ117 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የአፋር ክልላዊ መንግሥት በዚህ ወር የሚከበረውን የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ ለ117 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአፋር ክልላዊ መንግሥት በዚህ ወር የሚከበረውን የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ ለ117 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አሊ መሐመድ የክልሉ መንግሥት ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው በማረሚያ ቤት ያሳለፉ የሕግ ታራሚዎች ባሳዩት የሥነ ምግባር መሻሻል በይቅርታ በመፍታት ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ሲያደርግ እንደቆየ መናገራቸውን መንግሥታዊው የዜና ማሰራጫ ፋና ዘግቧል።

በሀገሪቱ በተጀመረው የአንድነትና ይቅርታ መንፈስ የተፈቱት የሕግ ታሪሚዎች የኅብረተሰቡን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በባለቤትንት መንፈስ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡

የተሰጠው ይቅርታ ከሙስናና ከአስገድዶ መድፍር ወንጀል ጋር ተያይዞ ተከሰው የፍርድ ውሳኔ የተሰጣቸው ታራሚዎችን አያካትትም፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG