በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፋር ውስጥ ለተገደሉት ተፈናቃዮች የሦስት ቀን ኀዘን ታወጀ


የአፋር ብሔራዊ ክልል ም/ቤት በጋሊኮማ መጠለያ ጣቢያ ሳሉ በህወሓት ጥቃት ህይወታቸውን አጡ ላላቸው ከ200 በለይ ንጹኃን ዜጎች የሦስት ቀናት የሃዘን ጊዜ አውጇል። አንድ ልጃቸውና የትዳር አጋራቸው በጥቃቱ የተገደሉባቸው አባት ጥቃቱን አረመናዊ ተገባር ሲሉ አውግዘውታል፡፡

በአፋር ጋሊኮማ መጠለያ ጣቢያ በተጠለሉ ተፈናቃዮች ላይ በተሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ከ40 እስከ 46 የሚደርሱ ሰዎች በዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ አመለክቷል፡፡

የክልሉን ም/ቤት አፈ ጉባኤ አሚና ሴኮን የጠቅሰው የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቃቱን ታሪክ የማይረሳው ነው ማለታቸውን አስንብቧል፡፡

ህወሓት ድንገት በከፈተው የከባድ መሳሪያ ጥቃት 107 ህጻናት፣ 89 ሴቶችና 44 አዛውንቶች ህይወታቸው ያለፈበት፣ በርካቶች የተጎዱበት፣ በመጋዘን ውስጥ የነበረ አስቸኳ የእርዳታ ምግብም ሙሉ በሙሉ የወደመበት መሆኑን የገለጹት አፈጉባኤዋ የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊን እንዲያወግዙና እንዲቃወሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሚዘልቀው የኃዘን ቀን የክልሉ መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተወስኗል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፋር ውስጥ ለተገደሉት ተፈናቃዮች የሦስት ቀን ኀዘን ታወጀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00


XS
SM
MD
LG