በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፋር የምርጫ ወረዳዎች ድልድል ቅሬታ


ምርጫ ቦርድ በአፋር ክልል የሚገኙ ሦስት ቀበሌዎችን በሶማሌ የምርጫ ክልል ውስጥ እንዲካተቱ ማድረጉን እንደማይቀበሉት፣ የአፋር ዴሞክራሲዊ ፍትሃዊ ፓርቲና የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አስታወቁ፡፡

ቦርዱ ማስተካከያ ካላደረገ በምርጫው እስካለመሳተፍ የሚደርስ ውሳኔ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ አሳስበዋል፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጣቢያዎች ሰዎች የምርጫ ጣቢያዎችን በቅርቡ አግኝተው እንዲመርጡ የተዘጋጁ እንጅ ምንም ዓይነት የአስተዳደር ወሰን መገለጫዎች አይደሉም ሲል ይመልሳል፡፡

በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ገዥው ፓርቲና አራት ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በአፋር ክልል ለመወዳደር በዝግጅት ላይ ባሉበትና የምርጫ ቅስቀሳ በተጀመረበት የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፍትሃዊ ፓርቲና የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በአፋር የምርጫ ወረዳዎች ድልድል ቅሬታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:28 0:00


XS
SM
MD
LG