በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፋር ክልል በተሰነዘረ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ


በአፋር ክልል እዋ አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ እያለ የሚጠራውና እራሱን የትግራይ ኃይል ብሎ የሚጠራው የህወሓት የታጠቀ ኃይል ትናንት ሰንዝሮታል በተባለ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ስድስት የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ሚኒሻ ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

በእዋ ከተማ አቅራቢያ ነዋሪ መሆናቸውን የሚናገሩ ግለሰብ በበኩላቸው ጦርነቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሰብዓዊ ቀውስ ማድረሱን ይናገራሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሁኔታ አስመልክተው ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ናቸው የተባሉት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ለችግሮች መፍትሔው "ጠላት ናቸው" ያሏቸውን ኃይሎች "ግበዓተ መሬት" መፈፀም ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

አፋር ክልል በተሰነዘረ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:29 0:00


XS
SM
MD
LG