በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነት ለተፈናቀሉ እርዳታ ማከፋፋል ተጀመረ


ደሴ
ደሴ

ጦርነት ከተቀሰቀሰባቸው የሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞንና አፋር አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሰፈሩ ከ20ሽህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች የእለት ደራሽ የምግብ ድጋፍ ማከፋፋል መጀመሩን የደቡብ ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በወልዲያና በጎንደር ግንባሮች እየተካሄደ ነው ባለው ጦርነት ሳቢያ የተፈናቀሉት ሰዎች ከሩብ ሚሊዮን እንደሚበልጥ ገልጿል፡፡

የደቡብ ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ መሳ ማሩ ለአሜረካ ድምጽ ራዲዮ እንደገለጹት ጦርነቱ መቀስቀሱን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የሚገባው የኅብረተሰብ ክፍል ከእለት እለት እየጨመረ ነው፡፡

በርካቶቹ ቤተሰብ ጋር የተወሰኑት በራሳቸው ወጭ አልጋ ይዘው መጠለላቸውን የጠቆሙት ኃላፊው የተወሰኑት ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በተዘጋጀላቸው መጠለያ ታቢያ እንዲያርፉ መደረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በጦርነት ለተፈናቀሉ እርዳታ ማከፋፋል ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00


XS
SM
MD
LG