ደሴ —
በአፋር ክልል እንደ አዲስ ተጀምሯል በተባለው ጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ሕክምና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የገለፀው ዱብቲ ሆስፒታል የህሙማኑ ብዛት ከሆስፒታሉ አቅም በላይ መሆኑን አስታወቀ።
የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር መሐመድ የሱፍ ሆስፒታሉ የቁሳቁና የሕክምና ባለሞያዎች እጥረት እንዳለበት ተናግረዋል።
በሌላ ዜና የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ ዛሬ አፋርን ጎብኝተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።