በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፋር ክልል መንግሥት የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች ከሰሰ


የአፋር ክልል መንግሥት የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች በንጹሃን የአፋር ተወላጆች ላይ ጥቃት ፈጸሙ ሲል ከሰሰ። ጥቃቱን ተከትሎ አዲስ አበባን ከጂቡቲ የሚያገናኘው መንገድ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር ተገልጿል። ጥቃቱ እንደተፈጸመ የተገለጸው አፋርና ሶማሌ በይገባኛል ከሚወዛገቡባቸው ሦስቱ ቀበሌዎች አንዷ በሆነቺው ኡንዱፎ ነው።

የሶማሌ ክልል በፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ከተወሰኑት 3ቱ ቀበሌዎች መካከል የአፋር ክልል ታጣቂዎች በሁለቱ ላይ ጥቃት ፈጽመው በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ ብሔር ተወላጆችን በመግደላቸውና የፌደራል መንግሥትም የሚጠበቅበትን ጥበቃ ባለመወጣታቸው ወደሦስተኛዋ ቀበሌ የክልሉን ልዩ ፖሊስ መላኩንና በቀበሌዋ ጥቃት ሊፈጽሙ የሞከሩ የአፋር ታጣቂዎችን መመለሱን አስታውቋል።

የሶማሌ ክልል በተጨማሪም መገናኛ ብዙሃን የአፋርና ሶማሌ ውዝግብን በሚዛናዊነት እየዘገቡ አይደለም ሲል ወቅሷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የአፋር ክልል መንግሥት የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00


XS
SM
MD
LG