አዲስ አበባ —
በ2002 ዓ.ም ምርጫ ወቅት ለተገደሉት ፍትሕ ሳይገኝ በ2007 እጩዎቹም ወከባና ማሳደድ በበርታቱን ነው ፓርቲው ያስታወቀው። የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ቃል-አቀባይ የፓርቲው ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ትላንት ባወጣው መግለጫ በአባሎቼ ላይ እየደረሱ ነው ያላቸውን በደሎች ዝርዝሯል። በተለይ የምርጫ ወቅትና ማግስት የወከባና የማሳደድ ጊዜ መሆኑን ነው ፓርቲው የጠቆመው። በደቡብ ክልል ደራሴ ወረዳ ተፈጸመ ያለውን የማሳደድ ተግባር በዋና ጸሃፊው አቶ አዳና ጥላሁን በተነበበው መግለጫ በምሳሌነት ጠቅሷል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።