በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አባሎቹ መታሠራቸውን መኢአድ አስታወቀ


የመንግሥት አካላት የታሠሩ የሉም ይላሉ፡፡

በደቡብ ክልል ጎፋ ልዩ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች 38 የፓርቲያቸው አባላት ሰሞኑን እንደታሠሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ለቪኦኤ እንደገለፁት ከታሠሩት መካከል ሃያ ሁለቱ ቀድሞ የገዥው ፓርቲ አባላት የነበሩና በቅርቡ ለቅቀው መኢአድን የተቀላቀሉ ናቸው፡፡

የእነርሱ መታሠርም “እስከአሁን ሲደረግ የነበረው ጫና ቀጣይ መሆኑን ይጠቁማል” ብለዋል፡፡

ፓርቲው ከጠቀሳቸው ከእነዚሁ ወረዳዎች አንዱ የሆነው የደምባ ጎፋ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዘለቀ ዶሣ የታሠሩ ሰዎች የሉም ብለዋል።

የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG