በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መኢአድ ከአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት እራሱን አገለለ


“የምክር ቤቱ አሠራር ዴሞክራሲያዊ አይደለም”

መኢአድ ከአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት እራሱን ያገለለው አሠራሩ “ዴሞክራሲያዊ ባለመሆኑ ነው” ሲሉ የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል አስታወቁ።

በ2002 ዓም ለተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ዝግጅት በምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ላይ ከመከሩ ፓርቲዎች አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ማቋቋማቸው ይታወሣል። ከምርጫው መጠናቀቅ በኋላ ግን ይህ የፓርቲዎች ምክር ቤት ሥራውን አቋርጦ ቆይቷል። በኋላ ላይ የቀጠለውም ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግና ሌሎች ፓርቲዎች በደንብና መመሪያዎቹ ላይ እንደገና ከተለያዩ በኋላ መሆኑን የምክር ቤቱ ምንጮች ገልፀዋል። ባለፈው አንድ ዓመት ተኩልም ከአሥር ያላነሱ መደበኛ ስብሰባዎችን ማድረጉን ጠቁሟል።

በዚህ መሃል ግን የምክር ቤቱ አባል ከሆኑ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እራሡን አግልሏል። የፓርቲው ፕሬዚደንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻወልን ለቪኦኤ ሲናገሩ ከምክር ቤቱና ከገዥው ፓርቲ ጋር የፈጠሩት ልዩነት አሁንም ባለበት እንደሆነ አብራርተዋል።

ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG