በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉዞ አድዋ የልዑካን ቡድን በወረኢሉ ከተማ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የጉዞ አድዋ ስድስት በጎ አድራጎት ማኅበር ዛሬ ወረኢሉ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረጎለታል፡፡

የጉዞ አድዋ ስድስት በጎ አድራጎት ማኅበር ዛሬ ወረኢሉ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረጎለታል፡፡

አዳማ ላይ በኦሮሞ አባቶችና አባገዳዎች ተመርቆ ጥር 1 ከአዲስ አበባ የተነሳው የልዑካን ቡድን 15 አባላትን ይዞ ዛሬ ሥምንት ሰዓት ገደማ ወረኢሉ ከተማ ደርሷል፡፡

የአካባቢው ኗሪዎች በባህላዊ አልባሳት ተውበው፣ ጥንታዊ የጦር መሳሪያዎችን ይዘውና በፈረስ ታጅበው ከሦስት ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ ነበር የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባል ያደረገላቸው፡፡

“ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት” በሚል መሪ ኃሳብ ጉዞውን ያሟሸው ልዑክ ካለፉት አምስት ተመሳሳይ መርኃ ግብሮች ለየት የሚያደርጉት ቁም ነገሮችን ይዞ ነው የተነሳው፡፡ መስፍን አራጌ ከስፍራው ዘገባ ልኳል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የጉዞ አድዋ የልዑካን ቡድን በወረኢሉ ከተማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG