በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዝየም ሥነ ጥበብ ሥራዎች ዳግም እንዲታዩ ማኅበሩ ጠየቀ


የኢትዮጵያ ሠዓልያንና ቀራፅያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ ወንድወሰን ከበደ
የኢትዮጵያ ሠዓልያንና ቀራፅያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ ወንድወሰን ከበደ

በዐዲስ አበባ ፒያሳ እየተገነባ ባለው በዐድዋ ድል መታሰቢያ ዐድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዚየም ውስጥ እንዲቀመጡ በታቀዱት የሥነ ጥበብ ሥራዎች ፕሮጀክት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ እንዳለው፣ የኢትዮጵያ ሠዓልያንና ቀራፅያን ማኅበር ገለጸ፡፡

የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ወንድወሰን ከበደ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በሙዝየሙ ውስጥ በሚቀመጡት የቅርፃቅርፅ፣ የሥዕል እና የሐውልት ሥራዎች ላይ፣ ውይይት አልተደረገም፡፡ 500 አባላት ያሉት ማኅበር፣ ከእንዲህ ዐይነት ሀገራዊ ፕሮጀክት መገለል የለበትም፤ ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ በቤተ መዘክሩ የሚቀመጡ 19 ሐውልቶች ሥራም፣ በቻይናዊ ተቋራጭ ግልጽ ባልኾነ መንገድ ለአንድ ግለሰብ እንደተሰጠ ተናግረዋል፡፡

ይህ አካሔድ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት መነሻ ማዕከል ተደርጎ ለሚከናወን ፕሮጀክት ትክክል እንዳልኾነ የተቹት ዋና ጸሐፊው፣ የዐዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳዩን ዳግም እንዲያጤነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በሒደቱ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዐድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዝየም ሥነ ጥበብ ሥራዎች ዳግም እንዲታዩ ማኅበሩ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:45 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG