ዋሽንግተን ዲሲ —
በዩኒቨርስቲውም አንድ ከምእራብ ጎጃም ደጋ ዳሞት ለትምህርት የሄደ ወጣት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ህይወቱ ማለፉን የአማራ ክልል አስታውቋል።
ይህን ተከትሎም በወልዲያ፣ ጎንደርና አምቦ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑን ተማሪዎች ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ፤ ጉዳዩ ወደ ለየለት የብሔር ግጭት እያመራ በመሆኑ በአስቸኳይ እልባት ሊያገኝ ይገባል ይላሉ። የአዲግራት ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ “እንደሚወራው አይደለም ሁኔታዎች ተረጋግተዋል ለግጭቱ ምክኒያት ናቸው የተባሉ ተማሪዎች በቁጥጥ ስር ውለዋል።” ብለዋል።
በትናንትናው ዕለት የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን ቀን ያከበረው የሰብዓዊ መብት ጉባዔ (ሰ.መ.ጉ)በኢትዮጵያ ብሔር ተኮር ግጭቶችና መፈናቅሎች በመባባሳቸው ሁኔታው ከመቼውም በላይ አስጊና አሳሳቢ ነው ሲል አስታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ