በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአድርቃይ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


በአድርቃይ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

በአድርቃይ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

በሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ ወረዳ ዓሊ ጣራ በተባለ ቀበሌ፣ ከትግራይ ክልል መጡ የተባሉ ታጣቂዎች፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሰነዘሩት ጥቃት፣ በሲቪል ሰዎች ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና ዘረፋም መፈጸሙን፣ የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የደረሰውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማረጋገጡን ያስታወቀው የአድርቃይ ወረዳም ኾነ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ ለጥቃቱ “የህወሓት ታጣቂዎች” ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የህወሓትን ቃል አቀባይ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም፣ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ከላሊ ሃጋዚ ግን፣ ከትግራይ ክልል ተነሥቶ ጥቃት የፈጸመ እንደሌለና ተፈጸመ ለተባለውም ጥቃት ክልላቸው ኃላፊነቱን እንደማይወስድ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG