አፍሪቃ ውስጥ ለቀጣይ ልማት ከአየር ንብረት ለውጥ አኳያ ተጨባጥ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ያተኮረው ስብሰባ የተካሄደው ዛሬ (ረቡዕ) አዲስ አበባ ላይ በመምከር ላይ ባለው በሰባተኛው የአፍሪቃ ልማት መድረክ ላይ ነዉ።
ውይይቱን ከመሩት ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ባለስልጣናት መካከል የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ አንዱ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ የበለፀጉ ሃገሮች መሪዎች ሕዝቡን ካየር ንብረት ለውጥ አኳያ በበቂ ሁኔታ ትምህርት እንዲያገኝ አላደረጉም፤ ለውጡን ለመቋቋምም ሆነ ለማለዘብ የሚያስችሉ ደፋር እርምጃዎችን ለመውሰድ አልቻሉም ሲሉ ወቅሰዋል።
በዚህም ምክንያት የአየር ንብረትን ለማሻሻል ሊሠሩ የሚገባ ተግባራት አልተሠሩም ብለዋል። በካንኩን-ሜክስኮ ውስጥ ከጥቂት ወራት በኋላ ከሚደረግ ዓለም አቀፍ የአየር ለውጥ ጉባዔም ተጨባጭ ውጤት እንደማይጠብቁ ጠቁመዋል። ስለሆነም አፍሪቃውያን ከአየር ንብረት ለውጡ ጋር ተስማምተው ለመኖር ያላቸውን ውስን ሃብት መጠቀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ለዝርዝሩ መለስካቸው አምኃ ከአዲስ አበባ የላከውን ዘገባ ያዳምጡ።