በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አበባ ባዲሳባ


አበባን በሥጦታና በመልካም ምኞት መግለጫነት መለዋወጥ በኢትዮጵያ እየተለመደ መጥቷል። ይህንኑ አጋጣሚ ወደ ገቢ ምንጭነት እየቀየሩ ካሉ ወጣቶች አንዷን እስክንድር ፍሬው ያስተዋውቀናል። *****

አበባ ሁሉም ነገር ነው፤ ከባህላችን የመዋሃዱን ያህል ግን በየበዓሉ የመለዋወጡ ነገር አልሰፋም፡፡ ለአንደበታችን የመቅረቡን፣ “ውበት፣ ፍቅር” የመባሉን ያህል የሚመረጥ ግዢ፣ የሚናፈቅ ስጦታ ሆኖ የዚያን ያህል አይታይም።

ስሜትን፣ የውስጥን ሊገልጹ የሚንደረደሩ አንዳንዶች ግን አበባን እንደውብ ቃላት፣ እንደመልካም ምኞት መግለጫ ይጠቀማሉ። በአንድ የአበባ መሸጫ መደብር ያገኘኋቸው ወይዘሮ ገነት ተሰማ እነዚህን ይወክላሉ።

___ “እኔ ገና የመጀመሪያ ጓደኛዬ የሰጠኝ ስጦታ አበባ ነው።”

___ ”ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የአበባ ጉዳይ አብሮዎት አለ ማለት ነው?”

___ ”አዎ አብሮኝ አለ፡፡ መጀመሪያ አበባ የሰጠኝ አሁን ባለቤቴ ነው። ሳንጋባ፣ ጓደኛዬ በነበረበት ሰዓት ከግቢያቸው ፅጌረዳ ቆርጦ ሰጠኝ፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው እንግዲህ ስለአበባ ስጦታነት የማውቀው።”

ይህን ያሉት ወይዘሮ ገነት ተሰማ አበባን እርሣቸው በስጦታ መስጠት ከጀመሩ ስድስት ሰባት ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ድሮ እስከዚህም አይደነቅም ነበር ያሉት ወይዘሮ ገነት ባለፉት ዓመታት ግን እየተለመደ መምጣቱን ይመሠክራሉ።

የአበባ ንግድን የገቢ ምንጫቸው ያደረጉም እየበረከቱ መጥተዋል፡፡ የዛሬ የህይወት በቀበሌ ዕንግዳም በተለይ በአዲስ አበባ ቁጥራቸው እየጨመረ ከመጣው የአበባ መደብሮች የአንዱ ባለቤት ናት። ወጣቷ ሜላት ጥላሁን ትባላለች፡፡ ወደዚህ ሥራ የገባችው ለአበባ ካላት ፍቅር በመነሣት ነው “ተቀጥሬ ስድስት ዓመት ሠርቻለሁ፡፡ አበባ መሥራት ያስተምሩ ነበርና አንድ ዘመዴ ወስዳ አስገባችኝ። ከልጅነት ጀምሬ ፍቅሩ ነበረኝ። አበባ በቅርብ ዓመታት በጣም እየተለመደ መጥቷል፡፡ ሰዉም በብዛት አበባ በስጦታ አበርክቶ ማስደሰትን ይመርጣል ባይ ነኝ፡፡”

“ለተማሪዎች ምረቃ፣ ለቫለንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን) ብዛት ያለው አበባ ይሸጣል” ብላለች ወጣቷ ባለመደብር። ደምበኛዋ ወይዘሮ ገነት ደምሴም ሜላት ለገዢዎች የትኛው አበባ ለምን ዓይነት ስጦታነት እንደሚገባ ደምበኞቿን እየረዳች እንደምታስተናግድ መስክረውላታል።

እስክንድር ፍሬው፥ ለቪኦኤ ከአዲስ አበባ

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG