በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት ጠፋ


ላፍቶ ክፍለ ከተማ
ላፍቶ ክፍለ ከተማ

በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ማንጎ ጨፌ ሌሎች በክፍለ ከተማው ስር ባሉ መንደሮች ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት ጠፋ።

መኖሪያ ቤቶቹ ይፈርሳሉ በመባሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወሰኑት አቤቱታ እያቀረቡ ባለበት ወቅት የመንግስት አፍራሽ ግብረኃይሎች ቤቱን ለማፍረስ የመብራት ትራንስፎርመር መንቀል እንደጀመሩና በዚህ መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደተፈጠር ነዋሪዎች ይናገራሉ።

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማምሻውን ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው በዚህ ግጭት ሁለት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና አንድ የወረዳ ስራ አስፈጻሚ ህይወት ማለፉን አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት ጠፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG