በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በይቅርታና በእርቅ ሁሉንም ወደነበረበት ሊመለስ ይገባል” - አቡነ ማቲያስ


“በይቅርታና በእርቅ ሁሉንም ወደነበረበት ሊመለስ ይገባል” - አቡነ ማቲያስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

“በይቅርታና በእርቅ ሁሉንም ወደነበረበት ሊመለስ ይገባል” - አቡነ ማቲያስ

“መጪው ጊዜ በይቅርታና በዕርቅ ሁሉንም ወደነበረበት የምንመልስበት እንዲሁም ሰላማችንን እና አንድነታችንን በፍትህ እና በእኩልነት የምንገነባበት ሊሆን ይገባል” ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ዛሬ አዲስ አበባ በተከበረው የጥምቀት ክብረ በዓል ላይ ተናገሩ።

በዓሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም መውረዱን ተከትሎ የሚከበር መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው የጠቆሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ሰላሙ እንደሚቀጥልም ተስፋቸውን ገልፀዋል።

በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በተመዘገበው በዚህ የጥምቀት በዓል ላይ ቁጥራቸው የበዛ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ታድመዋል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG