በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሂላሪ ብትመረጥ አዲስ ልምድ ታመጣለች" የፖለቲካ ሣይንስ ተማሪ

ሂላሪ ክሊንተን
ሂላሪ ክሊንተን

ዶናልድ ትራምፕ ከስደተኞች አንፃር የሚከተሉት ፖሊሲ እንደሚያሳስባቸው የገለፁት ቬኦኤ ያነገራቸው ኢትዮጵያውያን አስተያየት ሰጭዎች ነገ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂላሪ ክሊንተን ማሸናፋቸውን እንደሚመርጡ ገልፀዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ በትኩረት የሚከታተሉት ምሣሌ የሚሆን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በነገው ዕለት የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደበርካታ የዓለም አካባቢዎች ሁሉ በኢትዮጵያም ትኩረት ስቧል፡፡

ድምፅ የመስጠት መብት ባይኖራቸውም እንኳን ድጋፋቸውን የሚገልፁለት፤ እንዲያሸንፍ የሚመኙለት ዕጩ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

እስክንድር ፍሬው በተለይም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወጣቶችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኳል፡፡

"ሂላሪ ብትመረጥ አዲስ ልምድ ታመጣለች" የፖለቲካ ሣይንስ ተማሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

  • 16x9 Image

    እስክንድር ፍሬው

This item is part of
XS
SM
MD
LG