በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድነት ሰልፉን አካሄደ


የአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” መለያ /ሎጎ/
የአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” መለያ /ሎጎ/አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ
አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕግ ምክንያት የታሠሩ የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችም እንዲከበሩ ዛሬ አንድነት ለፍትኅና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የተካፈሉ ዜጎች ጠየቁ፡፡

ሰልፉን በአራት ኪሎ ወይም በሌሎች አደባባዮች ለማድረግ “ያደረግነው ጥረት በአዲስ አበባ አስተዳደር እምቢተኝነት አልተሣካም” ሲሉ የፓርቲው አመራር አባላት አማርረዋል፡፡

የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደው አዲስ አበባ ቀበና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድነት ለፍትኅና ለዴሞክራሲ ፅሕፈት ቤት አቅራቢያ ነው፡፡

ሰልፉን መስቀል አደባባይን ጨምሮ በሌሎችም የከተማይቱ አደባባዮች ማድረግ እንዲችል ለአዲስ አበባ አስተዳደር ያስታወቀው የአንድነት ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቷል፡፡

የዛሬው ሰልፍ በፅሕፈት ቤቱ አቅራቢያ የተወሰነውም ወደ አራት ኪሎ ሊያመራ የነበረው ሰልፈኛ በአዲስ አበባ ፖሊሶች እንዲቆም በመደረጉ ነው፡፡

ለፓርቲው የተፈቀደው የሰልፍ ቦታ “ጃን ሜዳ እንጂ ሌላ አይደለም” ሲሉ አንድንድ ፖሊሶች ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

የድምፅ ማጉያ የያዙ አንድ የፖሊስ አባልም “ወደ ተፈቀደላቸው ቦታ ብቻ እንድትሄዱ የፀጥታ ኃይሉ ይገልፃል” እያሉ በተደጋጋሚ ሲያሳስቡ ተሰምተዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” መለያ /ሎጎ/
የአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” መለያ /ሎጎ/

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አሥራት ጣሴ “በጃንሜዳ አቅራቢያ የጦር ሠፈር በመኖሩ እዚያ ሰልፍ ማድረግ ሕገወጥ ነው ስለዚህ አንሄድም” ሲሉ ለቪኦኤ አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም የተቃውሞ ሰልፉ እዚያው በፓርቲው ፅሕፈት ቤት አቅራቢያ ተካሂዷል፡፡

ሰልፈኞቹ በተለይ በፀረ-ሽብር ሕጉ ምክንያት የታሠሩ የፖለቲካ መሪዎች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG