በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፒያሣና መርካቶ የተወሰኑ ወርቅ ቤቶች ባለቤቶች ተወስደው የት እንዳሉ አይታወቅም


ፒያሣ አካባቢ ከሚገኙ ወርቅ ቤቶች መካከል ጥቂቶች
ፒያሣ አካባቢ ከሚገኙ ወርቅ ቤቶች መካከል ጥቂቶች

ማንነታቸው ያልተገለፀ ወይም ገና ያልተረጋገጠ ሰዎች ከትናንት በስተያ ሰኞ፣ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ፒያሣና መርካቶ የሚገኙ የወርቅ መደብሮች ውስጥ እየገቡ ንብረት መውሰዳቸው ተገልጿል።

“ለደኅንነታቸው በመሥጋት” ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የቪኦኤ ምንጮች የወርቅ ሱቆቹ ሠራተኞችና ባለንብረቶች “በፖሊስ እንደተያዙ፤ ንብረቶቻቸውም መወሰዳቸውንና ሱቆቻቸው እየተዘጉ” መሆኑን ጠቁመው አብዛኞቹም “የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን” ተናግረዋል።

እርምጃውን ወሰዱ የሚባሉት ግለሰቦች ሲቪል የለበሱና መሆናቸውንና ለመያዝ፣ ለመፈተሽም ይሁን ንብረት ለመውሰድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያልያዙ መሆናቸውን የገለፁት ምንጮች “ከሱቆቹ የወሰዱትን ንብረት ወደ ባንክ እንደሚያደርሱት ከመናገር ውጭ ስለአድራጎቶቻቸው፣ ወይም ወደየትኛው ባንክ እንደሚያስገቡ ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም መረጃ አለመስጠታቸውን ገልፀዋል።

“ተወስደዋል” የተባሉት ባለንብረቶችም ወደየት እንደተወሰዱና የት እንዳሉም የማይታወቅ ሲሆን እነዚህንና ሌሎችም ጥያቄዎች ይዘን ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽኖች መልስና ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ለጥቃቱ የተጋለጡት ሱቆች ብዛት ለጊዜው በውል ባይታወቅም ፒያሣ አካባቢ ሃያ የሚሆኑ የወርቅ መደብሮች ያለወትሮ ተዘግተው ማየታቸውን ምንጮቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG